ሁለተኛውን የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከወራት በፊት ያገባደደችው ኢትዮጵያ፣ በዓለም ባንክ እና ሌሎች መሰል ተቋማት የተመሰከረ ፈጣን የሚባል የኢኮኖሚያ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ጥቂት የአፍሪካ አገሮች መካከል ተጠቃሽ ናት፡፡ ለረጅም ዓመታት በኋላ ቀር የግብርና ምርት ላይ እና ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ተመርኩዞ ሲዘወር የነበረው ኢኮኖሚዋ በሂደት በአገር በቀል አገልግሎት ሰጪ ኢንቨስትመንት እና ከውጭ በሚገኝ የመዋዕለንዋይ ፍሰት ላይ…
ዕለታዊው የኮሮና ምርመራ ለምን ቀነሰ? | ዶ/ር አብርሃም አርአያ
ከቅርብ ቀናት ወዲህ ከጤና ሚኒስቴር በሚወጡ ዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ ሪፖርት ላይ የተጠቂ ቁጥር ላይ መቀነስ እየተመለከትን ነው:: ነገር ግን ይህ የቁጥር መቀነስ ከምን የመጣ ነው ብለን ስንጠይቅ፣ የምናገኘው መልስ ከምርመራ ቁጥር አብሮ መቀነስ ጋር ተያይዞ እናገኛዋለን:: መጀመሪያ በነበረው ሁኔታ የምርመራው አቅም አነስተኛ ቢሆንም በዚያው ልክ በቫይረሱ የሚጠቃውም ሰው ቁጥር በጣም ጥቂት የሚባል ነበር:: ከሚመረመረው ሰው…
የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስንብት
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: ፕሮፌሰር መስፍን በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለ10 ቀናት የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው እንደቆየና ባለፉት ጥቂት ቀናት ሕመማቸው እንደበረታ ከቤተሰቦቻቸው የተገነው መረጃ ያመለክታል:: ፕሮፌሰር መስፍን ከአባታቸው አቶ ወልደማርያም እንዳለ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ይመኙሻል ዘውዴ በሚያዚያ ወር 1922…
ብሔራዊ መግባባት እንዴት?
የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ከሥርወ መንግሥታዊ ወደ አብዮታዊ ከዚያም ወደ ዘውጋዊነት ባደረገው ታሪካዊ ጉዞ ምክንያት የጥንታዊነትና ዘመናዊነት፣ ዜግነታዊነትና ዘውጋዊነት፣ ባህላዊነትና ፖለቲካዊነት፣ ወዘተ… መንትያነቶች በአገሪቱ ብሔራዊ ማንነት ግንዛቤ፣ የብሔርተኝነት ፖለቲካና ጥናት ውስጥ በሰፊው ይንጸባረቃሉ፡፡ ስለዚህም ተቀዳሚው እርምጃ እነዚህን ጉራማይሌዎች የሚያስተናግድ ለአገር ግንባታው መሠረት የሚሆን ግልጽና አካታች ርዕዮተ ዓለም መንደፍ ይሆናል፡፡ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሕዝብን ከመንግሥት፣ እንዲሁም የመንግሥትን አካላት በአዎንታዊነት…
“በአዲስ አበባ የተፈፀመው ዝርፊያ በኢዜማ ጥናት ከተገለጸው በላይ ነው” | አቶ ኢዮብ መሳፍንት
በአዲስ አበባ ከተማ፣ በተለይም ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከተሾሙ ወዲህ ሕገ-ወጥ የመሬት ዝርፊያና የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕደላ እየተበራከተ መምጣቱን በርካታ ሰዎች ሲናገሩ ቆይተዋል:: ይህ የሕዝብ ምሬት ሰሚ ሳያገኝ ቢቆይም በቅርቡ ኢዜማ ይፋ ያደረገውን የጥናት ሪፖርት ተከትሎ ጉዳዩ ዋነኛ የውይይት አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል:: ኢዜማ ባዘጋጀው ጥናት እና ባቀረባቸው ምክረ ሐሳቦች ዙሪያ ከአቶ ኢዮብ መሳፍንት ጋር ቆይታ አድርገናል::…
“የፖለቲካል ኢኮኖሚ ለውጥ ያስፈልጋል” | ሳሙኤል ተክለ ኢየሱስ
በዚህ አገር የሥራ አጥ ቁጥር ለመብዛቱ ዋናው እና ትልቁ ምክንያት ወጣቱ ሥራ ፈጣሪ ለመሆን የሚያደርገው ጥረት ደካማ መሆኑ ነው:: አብዛኛው ወጣት የሚማረው በአንድ ተቋም ውስጥ ተቀጣሪ ለመሆን ነው:: አነስተኛ ቢዝነስ ብጀምር ትልቅ ቦታ እደርሳለሁ የሚለው አስተሳሰብ በአገራችን በአብዛኛው ወጣት ዘንድ እምብዛም አይስተዋልም:: በዚህ ረገድ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መጠነኛ ለውጦች መኖራቸው ባይካድም አሁንም በጣም ብዙ ይቀረናል::…
የትግራይና አማራ ልኂቃን ውድቀት | ብርሃኑ አበጋዝ (ዶ/ር)
የትግራይና አማራ ልኂቃን ውድቀት አገራችንን ውድ ዋጋ እያስከፈላት ነው፡፡ በዚህች አጭር ጽሑፍ ስለአማራና ትግራይ ወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ ስለሁለቱ ሕዝቦች ኅብረትና አንድነት መናገር አልፈልግም፤ በደንብ የሚታወቅ ስለሆነ፡፡ እነኝህ አንድም ሁለትም የሆኑ ሕዝቦች በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በፊደል፣ በሥነ-ልቦና አንድና ያው መሆናቸው የማያጠራጥር ሐቅ ስለሆነ፡፡ የእኔ አጀንዳ በእነኝህ የኢትዮጵያ ምሰሶዎች ላይ ልኂቃኑ ምን ያህል በደል እንዳደረሱባቸውና እያደረሱባቸው እንደሆነ የተወሰኑ ነጥቦችን…
የብሔር ግጭቶች ቀጣይነት | ደረጀ ዘለቀ (ዶ/ር)
የብሔር ግጭቶቹ ምንጭ ከፖለቲካ ሥርዓቱ ባሕርይ የሚቀዳ ነው፡፡ ለ27 ዓመት የተፈተለ ዘውግን መሠረት ያደረገ፣ ዘውግን መሠረት ማድረጉ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን አነጣጥሮ ሲቀጠቅጥ የኖረው ሥርዓት ነው ትልቁ የአገሪቱ ፈተና፡፡ የዘውገኝነት መሠረታዊ የሆነው አጥፊ ባሕርይው እንደተጠበቀ ሆኖ ጤነኛ በሆነ መልኩ ሊስተናገድ የሚችልበት ዕድል ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊ ውስጥ በተራመደበት ሁኔታ ማራመድ አስፈላጊ የማይሆንበት ሁኔታ ነበር፡፡ ዘውገኝነትን ለመኳል ኢትዮጵያዊነትን ማጠልሸትና…