እንወያይ

“የጥሬ ገንዘብ እጥረት የለም” | አቶ ፍቃዱ ደግፌ (የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና ዋና ኢኮኖሚስት)
እንወያይ, እንግዳ

“የጥሬ ገንዘብ እጥረት የለም” | አቶ ፍቃዱ ደግፌ (የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና ዋና ኢኮኖሚስት)

ሲራራ፡- ከሰሞኑ የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳለባቸው በመግለጽ ወጪ የሚፈልጉ ደንበኞችን   የሚመልሱ የግል እና የመንግሥት ባንክ ቅርንጫፎች ተበራክተዋል፡፡ የዚህ ችግር መሠረታዊ ምክንያቱ ምንድን ነው? አቶ ፍቃዱ፡- ስለዚህ ጉዳይ በእኛ በኩል የምናውቀው ነገር የለም፡፡ በእኛ መረጃ ጥሬ ገንዘብ የለም ወይም እጥረት ገጥሟል የሚል መረጃ የለንም፡፡ እኛ ያለን መረጃ ከአምናው የተሻለ ጥሬ ገንዘብ በገበያ ውስጥም ሆነ በባንክ ቤቶች…

“በትግራይ ክልል ያለው የሚና መደበላለቅ አፋጣኝ መፍትሔ ካልተሰጠው አደገኛ ነው” | አቶ አታክልቲ ወልደሥላሴ
እንወያይ, እንግዳ

“በትግራይ ክልል ያለው የሚና መደበላለቅ አፋጣኝ መፍትሔ ካልተሰጠው አደገኛ ነው” | አቶ አታክልቲ ወልደሥላሴ

በትግራይ ክልል ከተካሄደው “የሕግ ማስከበር” እርምጃ በኋላ ክልሉ በጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመራ ተደርጓል፡፡ ኮማንድ ፖስትም ተመድቧል፡፡ ሆኖም ክልሉን እንዲያረጋጉ በተመደቡት አመራሮች መሀከል የሚና መደበላለቅ እንዳለ እና በዚህም ምክንያት ሕዝቡ እየተማረረ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በተለያዩ ቦታዎች የተመደቡት አመራሮችም እየለቀቁ ነው፡፡ በቅርቡ ከኀላፊነታቸው የተነሱት የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ወልደሥላሴ ከእነዚህ አመራሮች አንዱ ናቸው፡፡ በምስጉን አመራርነታቸው ብዙ ሲባልላቸው…

“የኢትዮጵያ ሕዝብ የሴራ ፖለቲካ ሰለባ መሆኑ ማብቃት አለበት” | ሰይፈሥላሴ አያሌው (ዶ/ር)
እንወያይ, እንግዳ

“የኢትዮጵያ ሕዝብ የሴራ ፖለቲካ ሰለባ መሆኑ ማብቃት አለበት” | ሰይፈሥላሴ አያሌው (ዶ/ር)

በተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከብልጽግናና ኢዜማ ቀጥሎ በርካታ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን በማቅረብ ብዙዎችን ያስገረመው እናት ፓርቲ እንዴት ተመሠረተ? የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም ምንድን ነው? ከመንግሥት አወቃቀር አኳያስ የፓርቲው አቋም ምን ይመስላል? በእነዚህና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከፓርቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሰይፈሥላሴ አያሌው (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ሲራራ፡- ፓርቲያችሁ ከብልጽግና እና ከኢዜማ ቀጥሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው የምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን…

“በየደረጃው ከራስ ያነሰን ሰው የሚያስመርጥ ሥርዓት በተንሰራፋበት ሁኔታ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ዘበት ነው” | ፈቃደ አዘዘ (ዶ/ር)
እንወያይ, እንግዳ

“በየደረጃው ከራስ ያነሰን ሰው የሚያስመርጥ ሥርዓት በተንሰራፋበት ሁኔታ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ዘበት ነው” | ፈቃደ አዘዘ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ኀላፊዎች በዕውቀትም በልምድም ከእነሱ ያነሱ ሰዎችን የመመደብ የተለመደ አሠራር አለ፡፡ ይህ አሠራር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን የማይጠየቁና የማይደፈሩ፣ ብቸኛ አድራጊ-ፈጣሪ እንዲሆኑ የማድረግ ባሕርይ አለው፡፡ ይህም ኀላፊዎች ራሳቸው ሕግ (ከሕግ በላይ) እንዲሆኑ ስለሚያደርግ ተጠያቂነት እንዳይኖር፣ ይልቁንም በኀላፊዎችና በሠራተኞች መሀከል ያለው ግንኙነት የአለቃና ምንዝር ግንኙነት እንዲሆን በማድረግ የሠራተኞችን ፈጠራና የሥራ ተነሳሽነት ያዳክማል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ለምን…

“ኢትዮጵያዊያን አሁንም ከአእምሮ ቅኝ ግዛት ነጻ አልወጣንም” | ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ
እንወያይ, እንግዳ

“ኢትዮጵያዊያን አሁንም ከአእምሮ ቅኝ ግዛት ነጻ አልወጣንም” | ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ

ሲራራ፡- ኢትዮጵያ የረዥም ዘመን የአገረ መንግሥትነት ያላት አገር ሆና ሳለ ከታሪኳ ጋር አብሮ የሚሄድ ዘመናዊ እና/ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ያልቻለችው ለምንድን ነው? ፕሮፌሰር መሳይ፡- ብዙ የጻፍኩበት ጉዳይ ነው፡፡ እኔ ባደረግሁት ምርምር የደረስኩበት መደምደሚያ ኢትዮጵያዊያን የረዥም ዘመናት የአገረ መንግሥትነት ታሪክ ያለን መሆኑ የሚያኮራ ነው፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተደረገው የአገረ መንግሥት ግንባታም አይደለም አሁን ለምንገኝበት…

ወደ ሕዝብ የወረደው ልኂቃን ችግር | ታምራት ኀይሌ
እንወያይ

ወደ ሕዝብ የወረደው ልኂቃን ችግር | ታምራት ኀይሌ

“የፖለቲካ ሥልጣንን በአመጽ ከነጠቅህ በአመጽ ትገዛለህ፣ ልትወገድ የሚቻለውም በአመጽ ብቻ ነው።” – ፒክ ቦታ፣ የቀድሞው የአፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባጭሩ ለመግለጽ፣ ዴሞክራሲ በሕዝብ ፈቃድ ላይ የሚመሠረት፣ ሕዝቡ ሰላማዊና ነጻ በሆነ የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት በየተወሰኑ ጊዜያት በሚመርጣቸው ተወካዮች እና በራሱ ሕዝበ ውሳኔ በተደነገገው ማኀበራዊ ውል (social contract) ወይም ሕገ መንግሥት መሠረት የሚተዳደርበት አስተዳደር ማለት…

ስለ ፌዴራሊዝም እንወያይ | ዳንኤል ክንዴ (ዶ/ር)
እንወያይ

ስለ ፌዴራሊዝም እንወያይ | ዳንኤል ክንዴ (ዶ/ር)

በአንድ አገር ውስጥ ዘመናዊ አስተዳደርን ለመገንባትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ተመራጭነት ያለው አሕዳዊ ነው ወይስ ፌደራላዊ ሥርዓት? የሚለው ጥያቄ አሁንም አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ የትኛው አወቃቀር ይሻላል? ለምን? ለሚሉት ጥያቄዎች አንድ ያለቀለት ሁሉንም የሚያስማማ መልስ መስጠጥ አይቻልም፡፡ የሆነ ሆኖ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ክርክሩ ተጧጡፎ እንደቀጠለ ቢሆንም ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ፌደራላዊ ሥርዓት ነው በሚለው አጀንዳ ላይ ከሞላ ጎደል በሁሉም የአገራችን…

‹ዴማጎግሪ›፡- የተበላሸ ዴሞክራሲ | ሹምዬ ጌጡ (ዶ/ር)
እንወያይ

‹ዴማጎግሪ›፡- የተበላሸ ዴሞክራሲ | ሹምዬ ጌጡ (ዶ/ር)

የጥንት ግሪካውያን እምርታዊ የሥልጣኔ ዕድገት የዴሞክራሲን እሳቤ እና አስተዳደርን በመፍጠርና ለተቀረው ዓለም በማስተዋወቅ ቢጠቀስም፣ ግሪኮቹ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ የበዙ ጥርጣሬዎች ነበሯቸው፡፡ በተለይ ደግሞ እንደ ሶቅራጥስ እና ፕሌቶ ያሉ የፍልስፍና ሊቃውንት ዴሞክራሲን አብዝተው ይጠሉ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ እነዚህ በዴሞክራሲ ላይ የተሰነዘሩ ጥርጣሬዎች እና የሚታዩ ድክመቶች በሰፊው ሲንፀባረቁ  በገሐድ እየተመለከትን ያለበት ጊዜ ላይ ያለን ይመስለኛል፡፡ ለመሆኑ ዴሞክራሲ…

በአገራዊ አጀንዳዎች ላይ የዐሥሩም ክልል ፓርቲዎች ከሐሳብ አመንጪነት እስከ ትግበራ መሳተፍ አለባቸው!
እንወያይ

በአገራዊ አጀንዳዎች ላይ የዐሥሩም ክልል ፓርቲዎች ከሐሳብ አመንጪነት እስከ ትግበራ መሳተፍ አለባቸው!

መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም. “በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የሚያራምዱ የጋራ የፖለቲካ አቋሞቻቸው ላይ ስምምነት ተፈራረሙ” የሚለውን ዜና ከተለያዩ ሚዲያዎች ዘገባ ሰምተናል። ይህ አካሄድ በአማራና በኦሮሚያ ፓርቲዎች መካከል በጋራ አቋሞች ላይ ስምምነት ከተፈጠረ፣ በሌሎቹ ክልሎቹ አልፎ ተርፎም በአገሪቱ ያሉ ችግሮች መፍትሔ ያገኛሉ (by default) የሚል አንድምታዊ ትርጓሜን የሚያስተላልፍ ይመስላል። የሚገርመው ደግሞ የሁለቱ…

“ለተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥት አጥጋቢ ምላሽ እየሰጠ አይደለም” | ኢዜማ
እንወያይ

“ለተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥት አጥጋቢ ምላሽ እየሰጠ አይደለም” | ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥት አጥጋቢ ምላሽ እየሰጠ አይደለም አለ:: ኢዜማ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተፈጠሩ አለመረጋጋቶች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ከመንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ገልጿል:: ፓርቲው ኮሚቴዎችን አዋቅሮ የደረሰውን ጉዳት እና ተጎጂዎች ያሉበትን ሁኔታ እንዲሁም በመንግሥት…