በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ እየተሠራበት ያለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ በ1954 ዓ.ም የታወጀው ነው፡፡ ይህ ሕግ ዋና የወንጀል ሥነ-ሥርዓ ሕግ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ዋና ዓላማው በመሠረታዊ ሕግጋት ውስጥ የተረጋገጡት የዜጎች መብቶችና ግዴታዎች በፍትሕ ሂደት ውስጥ የሚመሩበት ሥርዓት ነው፡፡ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ብዙ ጊዜ በአገዛዞች ሲጠመዘዝ እንደነበር እና አገዛዞቹ በሚፈልጉበት መንገድ የወንጀል ጉዳይ አልሄድ…
ገንዘባችሁን በባንክ አስቀምጣችሁ [ብራችሁን] የዋጋ ንረት ይብላው ተብሎ ተፈርዶብናል
የኢትዮጵያ መንግሥት ባሳለፍነው ሳምንት በአገሪቱን የመገበያያ ገንዘብ ኖት ላይ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል ለዚህ እርምጃው ምክንያት ናቸው ያላቸውንም ጉዳዮች በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱ የሕገ-ወጥ ገንዘብን መቆጣጠር የሚለው ይገኝበታል፡፡ ሙስናንን ለመዋጋት የሚል ሐሳብም ቀርቧል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የመገበያያ ገንዘብ ቅያሪ ማድረግ ምን ያህል ያግዛል? የሚለውን ጉዳይ በሂደት አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሕገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር…
ከምርጫ ወደ አመጽ ወይስ በምርጫ ወደ ዴሞክራሲ?
ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ምክንያት ያራዘመችውን ስድስተኛውን አገር ዐቀፍ ምርጫ በተያዘው ዓመት ላይ ለማድረግ ዝግጅት ጀምራለች፡፡ በዘንድሮ ዓመት ለማድረግ የታሰበውን ምርጫ እስካሁን በአገሪቱ ከተደረጉ አምስት ምርጫዎች በተሻለ መልኩ ነጻ እና ፍትሐዊ ለማድረግ በሚል ቀድሞ የነበሩ የምርጫ ማስፈጸሚያ ደንቦች እና መመሪያዎች በአዲስ መልክ እንዲሻሻሉ ተደርገዋል፡፡ ምርጫ ቦርድም በአዲስ መልክ እንዲዋቀር ተደርጓል፡፡ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት…
ከግጭት ወደ ግጭት እንዳይሆን! | ዓለማየሁ ጉርሙ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያዊያን በርካታ መልካም ታሪካዊ አጋጣሚዎች አምልጠውናል፡፡ አሁን የሚታየው ለዴሞክራሲ ሽግግር ሊያግዝ የሚችል ታሪካዊ ዕድልም እንዳያመልጠን በእጅጉ ያሰጋል፡፡ ከአፈና አገዛዝ ተላቀን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ልንመሠርት ወደምንችልበት የሽግግር ዘመን ገባን ብለን ደስ ሲለን፣ ለውጡ መልኩን እንዲቀይርና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዲሄድ ከየአቅጣጫው መጠላለፍ እየታየ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ባለፈው የአፈና ዘመን እንኳ ባልታየ መልኩ በሺሕዎች የሚቆተሩ ኢትዮጵያዊያን እንደመጤና ባይተዋር እየተቆጠሩ እየተፈናቀሉ…