ሐሳብ

በኢትዮጵያዊነት አብሮ መኖር የውዴታ ግዴታ ነው! | ቴዎድሮስ ኀይሌ
ሐሳብ

በኢትዮጵያዊነት አብሮ መኖር የውዴታ ግዴታ ነው! | ቴዎድሮስ ኀይሌ

ኢትዮጵያዊያን በመቶም ይባል በሺሕ ዓመታት የአብሮነት ታሪካችን ውስጥ ያዳበርናቸው እና እንደ ሙጫ ያጣበቁን በጣም በርካታ የጋራ ዕሴቶች አሉን፡፡ ኢትዮጵያዊያን አንዳንዶች ሊነግሩን እንደሚሞክሩት ያለፈው ታሪካችን ሁሉ ጨለማ አይደለም፡፡ ይልቁንም እኛ ብቻ ሳንሆን መላው ጥቁር እና ሌሎች ጭቁን ሕዝቦች አብነት የሚያደርጓቸው በርካታ አኩሪ ዕሴቶች ያሉን ሕዝብ ነን፡፡ ስለሆነም በእነዚህ የጋራ ዕሴቶች ላይ ዘመኑን በዋጀ ሁኔታ ሌሎችን አዳዲስ…

“በጌታቸው መቃብር ላይ የብልጽግና አበባ ያብባል!” | አሳፍ ኀይሉ
ሐሳብ

“በጌታቸው መቃብር ላይ የብልጽግና አበባ ያብባል!” | አሳፍ ኀይሉ

ፊት አልባው ሰው ጌታቸው አሰፋ መቀበሩ ተሰማ፡፡ በእኔ አመለካከት የጌታቸውን ፊት ጨምሮ፣ እያንዳንዱ ሰው፣ እና እያንዳንዱ ነገር ሁለት ፊት አለው፡፡ ከሁለቱ ፊቶች አንዱን መርጦ ስለሱ ብቻ ማውራት ይቻላል፡፡ ግን የፊቱን ምሉዕ ምስል ማወቅ አይቻልም፡፡ የአብዛኛው ሰው አእምሮ ስለ አንድ ፊት አንድን ምስል ብቻ ማወቅ የሚሻ ነው፡፡ በአንድ ፊት ላይ ሁለት ተቃራኒ ገጽታዎች እንደሚኖሩ ማሰብ አይሻም፡፡…

መጪው ምርጫ ምን አርግዟል? | ዳዊት ዋበላ
ሐሳብ

መጪው ምርጫ ምን አርግዟል? | ዳዊት ዋበላ

“የኢትዮጵያ የምርጫ ፖለቲካ 1997 ዓ.ም. ላይ የቆመ ነው፤ ከዚያ በፊትም ከዚያ በኋላም የሕዝቡን ልብ የገዛ፣ ሕዝቡ በሙሉ ልቡ የተሳተፈበት እና አንጻራዊ የሆነ ነጻነት የነበረበት ምርጫ ኖሮ አያውቅም” ይላል የፖለቲካል ሳይንስ የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪው ነብዩ ሳሙኤል፡፡ እንደ ነብዩ ገለጻ፣ የኢትዮጵያን የምርጫ ፖለቲካ አስቸጋሪ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ በዚህች አገር ፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ የግራ አስተሳሰብ አሁንም ማዕከላዊ ቦታ…

ኢትዮጵያ እና የቦትስዋና ፈለግ | በሪሁን አዳነ
ሐሳብ

ኢትዮጵያ እና የቦትስዋና ፈለግ | በሪሁን አዳነ

ሻሹር ጉፕታ ስለ ቦትስዋና ተናግሮ አይጠግብም፡፡ አገሩ ደቡብ አፍሪካ “የቦትስዋና ፈለግ” ብሎ የሚጠራውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንድትከተል አጥብቆ የሚከራከረው ጉፕታ፣ ቦትስዋና ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች እየተገኘ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርቧል፡፡ በርእሰ-ጉዳዩ ላይ መጽሐፍም እያዘጋጀ ነው፡፡ ግን ለምን ቦትስዋና? የቦትስዋና ፈለግስ እንደምን ያለ ነው? የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ (SADC) መቀመጫ የሆነቸው ቦትስዋና በአህጉራችን ከሚገኙት በጣት የሚቆጠሩ ዲሞክራሲያዊ…

ለምን ዘመናዊ አገረ መንግሥት መገንባት ተሳነን? | ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር)
ሐሳብ

ለምን ዘመናዊ አገረ መንግሥት መገንባት ተሳነን? | ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር)

ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፤ ዴሞክራሲያዊ እና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ስለመገንባት ብዙ ሲነገርና ቆይቷል፡፡ ሆኖም አሁንም ዘመናዊ አገረ መንግሥት (State) መገንባት አልተቻለም፡፡ የኢትዮጵያን ህልውና ጠብቆና በኅብረተሰቡ መካከል ያሉ የዘውግ፣ የሃይማኖት፣ የመደብ፣ የአካባቢ ወዘተ… ልዩነቶችን በሚገባ ይዞ አገሪቱን ወደ ዝመና የሚወስድ የፖለቲካ  ኬሚስትሪ መቀመር አልተቻለም፡፡ የኢትዮጵያ ልኂቃን ትልቁ ውድቀት ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ፈተናም ይህ ነው፡፡ አገረ መንግሥታት ወሰኑ…

የጋና የዴሞክራሲ ሽግግር አብነት ፤ የእኛ ጉድለት ምንድን ነው? | ዳዊት ዋበላ
ሐሳብ

የጋና የዴሞክራሲ ሽግግር አብነት ፤ የእኛ ጉድለት ምንድን ነው? | ዳዊት ዋበላ

አንዲት አገር ዴሞክራሲያዊት አገር እንድትሆን የሚያስፈልጋት ምንድን ነው? ዴሞክራሲያዊ አገር ለመሆን ምን ምን ሁኔታዎች (requisites) ያስፈልጋሉ? ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር ለማድረግ በሚደረግ ሒደት (democratization) ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎች/ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? ወዘተ… የሚሉት ጥያቄዎች የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራንን ሲያከራክሩ የኖሩ፣ አሁንም የሚከራክሩ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ የዘመናዊነት ንድፈ-ሐሳብ (modernization theory) አቀንቃኝ የሆኑ የፖለቲካል ሳይንስና የሶሲዮሎጂ ምሁራን አንዲት አገር ዴሞክራሲያዊት አገር…

መጪዎቹ ሁለት አደጋዎች | ዳዊት ዋበላ
ሐሳብ

መጪዎቹ ሁለት አደጋዎች | ዳዊት ዋበላ

ኢትዮጵያ መግባት ባልነበረባት ጦርነት ውስጥ ግብታለች፡፡ አክራሪው የሕወሓት አመራር መሸነፉ ግልጽ ቢሆንም ይህ ጦርነት በኢትዮጵያ ወደፊት ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ግን እጅግ ከባድ ነው፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንያት የሚፈጠረውን ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ፣ ከዚያም አልፎ በሕዝቦች መሀከል የሚፈጥረውን ጠባሳ ለጊዜው እናቆየውና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ፣ ቢያንስ ሁለቱን እርስ በርሳቸው የሚመጋገቡ አደጋዎች እናንሳ፡፡ አንደኛው አደጋ ከመንግሥት…

“ትናንትም ዛሬም የኢትዮጵያ መሪ ጥያቄ የሥርዓት ጥያቄ ነው” | ዳንኤል ክንዴ
ሐሳብ

“ትናንትም ዛሬም የኢትዮጵያ መሪ ጥያቄ የሥርዓት ጥያቄ ነው” | ዳንኤል ክንዴ

“ያገሬ ሰው ገብር ሥራት ግባ ብየ ብለው እምቢ ብሎ ተጣላኝ፡፡ እናንተ ግን በሥራት በተገዛ ሰው አቸነፋችሁኝ፡፡” ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (Sven Rubenson: Acta Aethiopica vol II: Tewodros and his contemporaries 1855-1869, Addis Ababa and Lund, 1994, P.354) “… ነገር ግን የጠና መሠረት የሌለው ቤት ብዙ ዕድሜ ያገኛል ተብሎ እንደማይታመን እንዲሁም መንግሥታችን መሠረት ያለው ሥራት እስኪያገኝ ድረስ…

“ዐቢይ ይምራን!”  አምባገነንነትን የሚያነግሥ ክፉ ባህል | ብርሃኑ አበበ
ሐሳብ

“ዐቢይ ይምራን!” አምባገነንነትን የሚያነግሥ ክፉ ባህል | ብርሃኑ አበበ

ሕዝበኝነት ከተቋማትና ሥርዓታት (institutions) ይልቅ ‹የሕዝቡ አስተሳሰብና ዕውቀት› ይበልጣል የሚል መንፈስ አለው፡፡ ከልኂቃኑ ይልቅ ሕዝቡ፣ ከተቋማትና ሥርዓታት ይልቅ የሕዝቡ የራሱ የአኗኗርና አሠራር ዘይቤ ዓይነተኛ (authentic) እና ወሳኝ ነው ብሎ የማመን ዝንባሌ አለው ሕዝብኝነት፡፡ በጥቅሉ ሕዝበኝነት ከርዕዮተ ዓለም፣ ከተቋማዊ አሠራር እና ከሥርዓታት ጋር በተቃርኖ የቆመ ነገር ነው፡፡ ሕዝበኞች በተለያየ መልክ የሚገለጹ ቢሆንም ሕዝብን የሚያማልሉ ኮርኳሪ ቃላትን…

ቀማኛ ሲቪል ሰርቪስ | ያልተሻገርነው ፈተና | ዳንኤል ኪባሞ
ሐሳብ

ቀማኛ ሲቪል ሰርቪስ | ያልተሻገርነው ፈተና | ዳንኤል ኪባሞ

አገረ መንግሥት በአንድ ድንበሩ በታወቀ ጆግራፊያዊ ክልል ውስጥ፣ ዓላማውን ለማስፈጸም ኀይል የሚጠቀምና ብቸኛው የቅቡለ ኀይል ባለቤት የሆነ (legitimate use of force) አካል ማለት ነው፡፡ የአገረ መንግሥት መኖር፣ በዚያ ድንበሩ በታወቀ ጆግራፊያዊ ክልል ውስጥ ሥርዓተ አልበኝነት እንዳይሰፍን፣ ደካሞች በኀይለኞች እንዳይደፈጠጡ፣ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡና ንብረታቸው እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡ እዚህ ላይ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ዘመናዊ ወይም ጠንካራ አገረ መንግሥት…