“እውነተኛ ልማት እንዲመጣ ከተፈለገ እውነተኛ ውድድር የሚፈጠርበትን ዕድል ማመቻቸት ያስፈልጋል” | አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ
ዜና

“እውነተኛ ልማት እንዲመጣ ከተፈለገ እውነተኛ ውድድር የሚፈጠርበትን ዕድል ማመቻቸት ያስፈልጋል” | አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ የሚያስተላልፉት ባንኮች ናቸው:: ብሔራዊ ባንክ ጉልበቱንም አቅሙንም አስተባብሮ ቁጥጥር ክትትል የሚያደርገው ባንኮችን ነው:: ለባንኩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ትርጉም የሚሰጡ እየሆነ አይደለም:: በአብዛኛው በዓለም አገር ውስጥ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ክትትል እና ቁጥጥር የሚደረገው በብሔራዊ ባንክ በኩል የሚከወን አይደለም:: ከ27 ዓመት በፊት የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በነበርኩበት ጊዜ የወቅቱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ለይኩን ብርሃኑ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች እንዲቋቋሙ አዋጁ ሲረቀቅ ስለ ጉዳዩ ሐሳብ ጠይቀውኝ ነበር:: የኢንሹራንስን ክትትል እና ቁጥጥር በምን መልኩ እናድርገው በሚል ላነሱልኝ ጥያቄ፣ የተቋማቱ ቁጥጥር በብሔራዊ ባንክ ውስጥ አይሁን ራሱን የቻለ የኢንሹራንስ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን እንዲያቋቁሙ ነበር የመከርኩት:: በአፍሪካም ቢሆን በዚያ መንገድ ነው ጠንካራ የኢንሹራንስ ተቋማት የተፈጠሩት::

October 13, 2020

About Author

admin


Leave a Reply

Your email address will not be published.