ርእሰ አንቀጽ
ከውጭ ወራሪ የተከላከልናትን አገር ከውስጥ ጭቆና ማላቀቅ ለምን ተሳነን?
የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. 84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ታስቦ ውሏል፡፡ 125ኛውን የዓድዋ ድል በዓልም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ ይህችን አገር ከውጭ ወረራ ጠብቆ ለማቆት የተከፈለው መስዋዕትነት እጅግ የሚያኮራ ነው፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያዊያን አገራችንን ከውጭ ወራሪ ጠብቆ በማቆየት ረገድ ደማቅ ታሪክ ያለን ብንሆንም ከውጭ ወራሪ የተከላከልናትን አገር ከውስጥ ጭቆና ማላቀቅ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ...